መዝሙር 18:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ለእኔ ብርሃኔ ነህ፤ አንተ አምላኬ ጨለማዬን ታበራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴን ታበራለህ፤ አምላኬ፤ ጨለማዬን ያበራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዐይን ግን ታዋርዳለህ። |
ይሁን እንጂ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም በሰላም እንዲጠብቅ አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው፥
“ዕውሮችን ሄደውበት በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ቀድሞ ባላወቁትም መንገድ እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸው የተጋረደውንም ጨለማ ወደ ብርሃንነት እለውጣለሁ፤ ወጣገባ የሆነውንም ስፍራ አስተካክላለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እኔ የምፈጽማቸው ናቸው፤ አልተዋቸውምም።
የሚሰጣት ፍርድ እንደ ንጋት እስኪፈነጥቅና መዳንዋም እንደሚነድ ችቦ እስኪበራ ድረስ፥ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ከማሰብ አላርፍም።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።