ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።
መዝሙር 18:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንደበቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳብም ሁልጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድኤቴ መድኀኒቴም። |
ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።
እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል።
እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?
ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደ ጐሽ ይዋጋላቸዋል፤ ጠላቶቻቸው የሆኑትን ሕዝቦች ይቦጫጭቅላቸዋል፤ አጥንቶቻቸውን ያደቃል፤ ቀስቶቻቸውንም ይሰባብራል።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።
እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።”