Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 37:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤ በድምፁም ግርማ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁ በተሰማ ጊዜ፣ መብረቁን የሚከለክል የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከበስተኋላው ድምፅ ያገሣል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጉዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በስ​ተ​ኋ​ላው ድምፅ ይጮ​ኻል፤ በግ​ር​ማ​ውም ድምፅ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ድም​ፁም በተ​ሰማ ጊዜ ሰዎች እን​ዲ​ጠፉ አያ​ደ​ር​ግም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 37:4
12 Referencias Cruzadas  

እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?”


ዝናብና ለነጐድጓዳዊ መብረቅ ሥርዓትን በደነገገ ጊዜ፥


ከአፉ የሚወጣውን ድምፅ ስሙ እንደ ነጐድጓድ የሚያጒረመርመውን ቃሉን አድምጡ።


መብረቁን ከሰማይ በታች ሁሉ ያሠራጫል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ይልካል።


እግዚአብሔር አስደናቂ በሆነ ድምፁ ነጐድጓድን ያሰማል፤ እኛ ልንረዳው የማንችል ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል።


ለመሆኑ ኀይልህ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ኀይል የበረታ ነውን? ድምፅህስ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነውን?


ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው።


ከሰማያት በላይ ወዳለው ሰማይ ለሚወጣው ዘምሩ፤ በሚያስገመግም ብርቱ ድምፅ ሲናገርም አድምጡት።


የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በሰማያዊ ግርማው አንተን ለመርዳት በሰማይና በደመና ላይ እንደ እኛ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ማንም የለም


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos