Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 37:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከበስተኋላው ድምፅ ያገሣል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጉዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤ በድምፁም ግርማ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁ በተሰማ ጊዜ፣ መብረቁን የሚከለክል የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በስ​ተ​ኋ​ላው ድምፅ ይጮ​ኻል፤ በግ​ር​ማ​ውም ድምፅ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ድም​ፁም በተ​ሰማ ጊዜ ሰዎች እን​ዲ​ጠፉ አያ​ደ​ር​ግም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 37:4
12 Referencias Cruzadas  

የምድር ነገሥታት፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ለጌታም ዘምሩ።


“ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ ጌታ ያለ ማንም የለም።


እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?”


የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጉርምርምታ አድምጡ።


መብረቁንም ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ወደ ምድርም ዳርቻ ይሰድዳል።


እግዚአብሔር በአስደናቂ ሁኔታ በድምፁ ያንጐደጉዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።


ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥


እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጉዳለህን?


ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios