አምላክ ሆይ! ልመናዬን ስለምትሰማ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።
አቤቱ፥ ሰምተኸኛልና ወደ አንተ ጠራሁ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ቃሌንም ስማ።
በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ በቤተ መቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
ምንም ያኽል ብትበሳጩ ኃጢአት አትሥሩ፤ በምትተኙበት ስፍራ በጸጥታ ልባችሁን መርምሩ።
እኔ ግን ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እጣራለሁ፤ እርሱም ያድነኛል።
አንተ ለጸሎቴ መልስ ስለምትሰጥ በመከራ ጊዜ ወደ አንተ እጮኻለሁ።
እባክህ ጸሎቴን ስማ! ጩኸቴንም አድምጥ!
አምላክ ሆይ! ሰናክሬም! እንዴት አድርጎ አንተን ሕያው አምላክን እንደ ዘለፈ ተመልከት።
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦራውያን እጅ በመታደግ አድነን።”