Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 37:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አምላክ ሆይ! ሰናክሬም! እንዴት አድርጎ አንተን ሕያው አምላክን እንደ ዘለፈ ተመልከት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አቤቱ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብልና ስማ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህን ክፈትና እይ። ሰናክሬም ሕያው አምላክን ለመሳደብ የላከውን ቃል ሁሉ ስማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጌታ ሆይ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ ጌታ ሆይ፥ ዓይንህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ለመገዳደር የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ተመ​ል​ከት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዓይንህን ክፈትና እይ፥ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 37:17
17 Referencias Cruzadas  

ምናልባት እግዚአብሔር መከራዬን አይቶ በእርሱ ርግማን ፈንታ በረከትን ይሰጠኝ ይሆናል።”


አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤


“አምላኬ ሆይ፥ በዚህ ስፍራ ወደሚቀርበው ጸሎት ዐይኖችህ የተገለጡ ጆሮዎችህም አጣርተው የሚያደምጡ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ።


ይህን ቤተ መቅደስ እጠብቀዋለሁ፤ በዚህ ቤተ መቅደስ የሚቀርበውንም ጸሎት ሁሉ እሰማለሁ።


እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ይጠብቃል፤ እንደ ነገሥታትም በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ ለዘለዓለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።


ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ።


አምላክ ሆይ! ልመናዬን ስለምትሰማ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።


በጽድቅህ ከችግር እንዳመልጥ አድርገህ አውጣኝ አድምጠህም አድነኝ።


አምላክ ሆይ! ጠላቶች በአንተ ላይ የሚሳለቁት እስከ መቼ ነው? ስምህንስ የሚዳፈሩት ያለማቋረጥ ነውን?


አምላክ ሆይ! ተነሥ! ስምህን የሚዳፈሩትን ተከላከል! እነዚህ ሞኞች ቀኑን ሙሉ በአንተ ላይ እንደሚሳለቁ ተመልከት።


ጌታ ሆይ! ጐረቤቶቻችን በአንተ ላይ ስለ ተዘባበቱ በሰባት እጥፍ ተበቀላቸው።


የአሦር ንጉሥ ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ስለሚተርፉት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ይመለከታሉ፤ ጆሮዎቹም ጸሎታቸውን ለመስማት ተከፍተዋል፤ በክፉ አድራጊዎች ላይ ግን ጌታ የቊጣ ፊቱን ያሳያል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos