እግዚአብሔርን አመስግኑ! ከላይ ከሰማያት አመስግኑት።
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በላይ በአርያም አመስግኑት።
ሃሌ ሉያ። ጌታን ከሰማያት አመስግኑት፥ በአርያም አመስግኑት።
እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በአርያም ያመሰግኑታል፤
በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
እግዚአብሔር ይመስገን! ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
ሰማይና ምድር፥ ባሕሮችና በውስጣቸው የሚኖሩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግኑት።
እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚያጽናና እና ለሚሠቃዩትም ስለሚራራ ሰማያት ሆይ! ዘምሩ፤ ምድር ሆይ! ደስ ይበልሽ፤ ተራራዎች ሆይ! እልል በሉ።
ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።