የሚንገዳገዱትን ይደግፋል፤ የወደቁትንም ያነሣቸዋል።
እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤ የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።
ጌታ በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፥ ጌታ የሚወድቁትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ ያጎነበሱትንም ያነሣቸዋል።
እድን ዘንድ ደግፈኝ፤ ሁልጊዜም ሕጎችህን እፈጽማለሁ።
የዕውሮችን ዐይን ያበራል፤ የወደቁትን ያነሣል፤ ጻድቃንን ይወዳል።
እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም።
ጐበጥኩ፤ እጅግም እያጐነበስኩ ሄድኩ፤ ቀኑን ሙሉ በትካዜ አሳለፍኩ።
እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤ ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
“ለመውደቅ ተቃርቤአለሁ” ባልኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደግፎ አቆመኝ።