እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ያኽል የምትንከባከበው ሰው ምንድን ነው? ይህን ያኽልስ የምታስብለት የሰው ልጅ ምንድን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?
አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው? ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ምስጋናውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታላቅነቱም ዳርቻ የለውም።
“ሰው ንጹሕ ሊሆን ይችላልን? ሥጋ ለባሽስ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን?
“ግምት ትሰጠው ዘንድና ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? እርሱንስ ትጐበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
ከመላእክት በጥቂቱ ብታሳንሰውም፥ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፤
እንግዲህ ትንፋሹ አፍንጫው ላይ በሆነች በሟች ሰው መተማመናችሁ ይቅር፤ እርሱ ለምንም አይጠቅምም።
እንዲያውም በቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎአል፦ “አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ለእርሱስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?