እግዚአብሔር ሆይ! ከክፉዎች ኀይል ጠብቀኝ፤ እኔን ለመጣል ከሚያቅዱ ከዐመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፤ እግሮቼንም ለመጥለፍ ከሚያደቡ ዐመፀኞች ሰውረኝ።
ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፥ ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ አለ።
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
የትዕቢተኞች እግር እንዲረግጠኝ፥ የክፉዎች እጅ እንዲአባርረኝ አታድርግ።
አንተ አታላይ ሰው ሰዎችን የሚጐዳ ቃል መናገር ትወዳለህ!
እፉኝት ጆሮውን የሚደፍነው የእባብ አፍዛዦችን ድምፅ፥ ወይም የአስማተኞችን ድግምት ላለመስማት ነው።
አምላኬ ሆይ! ከክፉ ኀይልና ርኅራኄ ከሌለው ዐመፀኛ እጅ አድነኝ።
ለበደለኛው ማዳላትና ንጹሕ ሰው ትክክለኛ ፍትሕ እንዳያገኝ ማድረግ ተገቢ አይደለም።