ከዚህ በኋላ “ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ፤ በእግሩ ማረፊያ ሥር እንስገድ” አልን።
“ወደ ማደሪያው እንግባ፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።
ወደ ማደሪያዎቹ እንግባ፥ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስገድ።
ወደ ውስጥ ገብቼ እግዚአብሔርን እንዳመሰግን የቤተ መቅደስን በሮች ከፈቱልኝ።
“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ!” ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
እኔ ግን በታላቅ ምሕረትህ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ወደ ቤተ መቅደስህ በአክብሮት እሰግዳለሁ።
ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!
አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑት! በእግሩ ማረፊያ ሥር ስገዱ! እርሱ ቅዱስ ነው።
አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና፥ እርሱን አክብሩት፤ በተቀደሰው ተራራም ላይ ስገዱለት፥
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
እግዚአብሔር በቊጣው ጽዮንን ምንኛ አዋረዳት! ወደ ሰማይ ከፍ ብላ የነበረችውን የእስራኤልን መመኪያ ወደ ምድር ጣላት፤ በቊጣው ቀን የእግሩ ማሳረፊያ መሆንዋን ሊያስታውስ አልፈቀደም።