እስራኤል ሆይ! ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ!
እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እስራኤል በጌታ ይታመን።
“ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥ ወደ መኝታዬም አልጋ አልወጣም፥
እኛ ግን በሕይወት ያለነው ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እናመሰግነዋለን። እግዚአብሔር ይመስገን!
ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና ወደ ቤትህም ስትመለስ ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።
እስራኤል ሆይ! ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነና ሰዎችንም የማዳን ኀይል ያለው ስለ ሆነ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነለትና በአምላኩ በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረገ ሰው ደስ ይበለው፤
ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።