መዝሙር 125:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች በጻድቃን ምድር ላይ የሚዳኙት ለብዙ ጊዜ አይደለም፤ አለበለዚያ ጻድቃንም ክፉ ማድረግን ይጀምራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን እጃቸውን ለክፋት እንዳያነሡ፣ የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስተኞችም ሆን። |
በሰው ከሚደርሰው ፈተና በቀር ሌላ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም፤ በምትፈተኑበትም ጊዜ የምትታገሡበትን ኀይል በመስጠት ከፈተናው የምትወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላችኋል።
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።
ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤