መራብና መጠማትም አይደርስባቸውም፤ የሚያቃጥል ነፋስ ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም፤ ይህም የሚሆነው የሚራራላቸው እርሱ የውሃ ምንጭ ወደሚገኝበት ቦታ ስለሚመራቸው ነው።
መዝሙር 121:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አያደርሱብህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይ በቀን አይመታህም፥ ጨረቃም በሌሊት እንዲሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢየሩሳሌም ደኅንነትዋን፥ ተነጋገሩ። ስምህን ለሚወድዱ ደስታቸው ነው። |
መራብና መጠማትም አይደርስባቸውም፤ የሚያቃጥል ነፋስ ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም፤ ይህም የሚሆነው የሚራራላቸው እርሱ የውሃ ምንጭ ወደሚገኝበት ቦታ ስለሚመራቸው ነው።
ፀሐይ ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ ላከ፤ የፀሐዩም ሐሩር ራሱን ስላቃጠለው ዮናስ ተዝለፈለፈ፤ ሞትንም በመመኘት “ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል” አለ።