መዝሙር 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣ ስለ ድኾችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላሳችንን እናበረታለን፥ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል። |
ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።
እንደገናም በዓለም ያለውን የፍርድ መጓደልና ግፍ ተመለከትኩ፤ የተገፉ ጭቊኖች የሚያጽናናቸው አጥተው ያለቅሱ ነበር፤ የፈላጭ ቈራጭነት ሥልጣን በገዢዎቻቸው እጅ ስለ ሆነ የሚረዳቸው አላገኙም።
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።
እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ችግር ሲደርስባቸው እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፤ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል።
ከእኔ ርቀው ወደ ከንቱ አምልኮ ተመለሱ፤ ዓላማውን እንደሚስት እንደ ተበላሸ ቀስት ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ክፉ ነገርን ከመናገራቸው የተነሣ በሰይፍ ተመተው ይሞታሉ፤ በግብጻውያንም ዘንድ መዘባበቻ ይሆናሉ።”
ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።