ባሕር ይህን አይቶ ሸሸ፤ የዮርዳኖስም ወንዝ ውሃ ማፍሰሱን አቁሞ ወደ ኋላው ተመለሰ።
ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትና መከራ አገኘኝ።
ውሃውን በገሠጽከው ጊዜ ከፊትህ ሸሸ፤ የትእዛዝህን ድምፅ በሰማ ጊዜ በፍጥነት ሮጠ።
ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው።
ምንጮችና ጅረቶች እንዲፈስሱ አደረግህ፤ ታላላቅ ወንዞችን ግን አደረቅህ።
አምላክ ሆይ! ውሃው አንተን ባየ ጊዜ ፈራ፤ ጥልቅ ባሕሮችም ተንቀጠቀጡ።
ደመናዎች ዝናብን አዘነቡ፤ ነጐድጓድ በሰማይ አስገመገመ፤ የመብረቅ ፍላጻዎችህም ከላይ ከሰማይ አንጸባረቁ።
ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ባሕሩን ወደ ኋላ መለሰው፤ ነፋሱም ሌሊቱን ሙሉ በመንፈሱ፥ ባሕሩን ወደ ደረቅ ምድር ለወጠው፤ ውሃውም ከሁለት ተከፈለ፤
በቊጣህ እስትንፋስ፥ ውሃው ወደ ላይ ተቈለለ፤ እንደ ግድግዳም ቀጥ ብሎ ቆመ፤ በጥልቅ ስፍራ ያለውም ውሃ፥ ረግቶ ጠጠረ።
ለራሱ ዘለዓለማዊ ስም ይሆን ዘንድ በፊታቸው ውሃን ለመክፈል ክብርን የተመላ ኀይሉን በሙሴ ቀኝ በኩል እንዲራመድ ያደረገው የት አለ?
አንተ ባሕሩን በፈረሶችህ በምትረጋግጥበት ጊዜ ጥልቁ ባሕር ይናወጣል።