La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 113:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ይመስገን! እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ!

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሃሌ ሉያ። የጌታ አገልጋዮች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የጌታንም ስም አመስግኑ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም ወገን ከጠ​ላት ሕዝብ በወጡ ጊዜ፥

Ver Capítulo



መዝሙር 113:1
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ይመስገን! እግዚአብሔርን የሚፈራና ትእዛዞቹንም በመፈጸም እጅግ ደስ የሚለው ሰው እንዴት የተባረከ ነው!


እናንተ አገልጋዮቹ! በሌሊት በመቅደሱ የምታገለግሉት ሁሉ፥ ኑ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


እናንተ ሌዋውያን እግዚአብሔርን አመስግኑ! እግዚአብሔርን የምታከብሩ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


እግዚአብሔር ሆይ! ፍጡሮችህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ ሕዝቦችህም ሁሉ ያወድሱሃል።


እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤ በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።


የአገልጋዮቹም ዘሮች ይወርሱአታል፤ እርሱን የሚወዱ ሁሉ እዚያ ይኖራሉ።


ከዚህ በኋላ “እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ታናናሾችም ታላላቆችም አምላካችንን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ።