መዝሙር 111:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርጎአል፤ በእርሱ አስደናቂ ሥራዎች የሚደሰት ሁሉ ያስባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ሥራዎች ታላላቅ ናቸው፥ ደስ በሚሰኙባቸው ሁሉ ይፈለጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የጻድቃን ትውልዶች ይባረካሉ። |
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገር ጊዜ በመወሰን ሁሉን ነገር ውብ አድርጎ ሠርቶታል፤ ዘለዓለማዊነትንም በሰው ልቡና አሳድሮአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ያውቅ ዘንድ ለሰው የተሰጠው ዕውቀት ሙሉ አይደለም።
ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥ የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው? ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ በሚዛን የሚመዝን ማን ነው?
“እግዚአብሔር የሚያሳየው ተአምር እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ የሚፈጽመው ድንቅ ሥራ እንዴት ብርቱ ነው! እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
የማይለካው ታላቅ ኀይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ታውቁ ዘንድ እጸልያለሁ፤ ይህንንም ታላቅ ኀይሉን በተግባር ያሳየው ከሞት አስነሥቶ በሰማይ በቀኙ ባስቀመጠው በክርስቶስ አማካይነት ነው።
የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤