እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
ሃሌ ሉያ። በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
ሃሌ ሉያ! በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም ጌታን በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ! ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡ ሁሉ አሜን አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመስግኑ።
በሕዝብ ጉባኤ መካከል ታላቅነቱንም ያብሥሩ፤ በሽማግሌዎች ሸንጎ ያመስግኑት።
እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በአሕዛብ መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
ድምፄን ከፍ አድርጌ ለእግዚአብሔር ክብር እሰጣለሁ፤ በሕዝብ ጉባኤ መካከል አመሰግነዋለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ በመላእክት ፊት ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ! ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት!
እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት አመስግኑት! እናንተ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንተ የእስራኤል ዘሮች ሁሉ በፍርሃት ከፍ ከፍ አድርጉት!
ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎች ፊት ሆኜ፥ የተሳልኩትን ስለት እፈጽማለሁ።
በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።
በሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤ መካከል እግዚአብሔር የተፈራ ነው፤ በዙሪያውም ካሉት ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው።
አምላክ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ያደረግኸውንም ድንቅ ነገር ሁሉ እናገራለሁ!