Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 106:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔርን አመስግኑ! ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 106:1
16 Referencias Cruzadas  

በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ሕይወት እግዚአብሔር ከእናንተ የሚፈልገው ይህን ነው።


እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ ያደረገውንም ሁሉ ለአሕዛብ ንገሩ።


ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ቸር ስለ ሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ።


ይህንንም ሁሉ ማድረጉ ሕዝቡ ድንጋጌውን እንዲጠብቁና ሕጉንም እንዲፈጽሙ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!


ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


“እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” የሚለውን መዝሙር በመቀባበል ለእግዚአብሔር ክብር ዘመሩት፤ የቤተ መቅደሱ መሠረት የማኖር ተግባር ስለ ተጀመረም እያንዳንዱ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እልል በማለት እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር።


ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።


አንተ ቸር ስለ ሆንክ ቸር የሆነውን ታደርጋለህ፤ ሕጎችህን አስተምረኝ።


ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤ ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።


በዚያም ከእነርሱ ጋር ሄማን፥ ይዱታን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ፍቅር በማሰብ ዘወትር ለእርሱ የምስጋና መዝሙር ያቀርቡ ዘንድ ሌሎችም በተለይ የተመረጡ ሰዎች ነበሩ፤


ደግ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ! ቸር ስለ ሆነ ለስሙ ዘምሩ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios