መዝሙር 110:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፤ በሚቈጣበት ጊዜ ነገሥታትን ድል ነሥቶ ይሰባብራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ በቀኝህ ነው፤ በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በቀኝህ፥ ነገሥታትን በቁጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል። |
በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤ ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”