እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በአሕዛብ መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ።
በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እንዲሁ፥ እኔም ማለዳን ልቀስቅሰው።
በጥል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተዋጉኝ።
መንግሥታት ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት! ሕዝቦች ሁሉ አመስግኑት!
የስምህን ታላቅነት ለወገኖቼ እናገራለሁ፤ እነርሱ በተሰበሰቡበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤
እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።
በሕዝቦች መካከል “እግዚአብሔር ንጉሥ ነው! ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ በትክክል ይፈርዳል” በሉ።
የጽዮን ልጅ ሆይ! ዘምሪ! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ዘምሩ! እልልም በሉ! የኢየሩሳሌምም ሕዝብ ሆይ! በሙሉ ልባችሁ ደስ ይበላችሁ! ሐሴትም አድርጉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ሰብስቤ ወደ ሀገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ ንብረታችሁን ሁሉ ዐይናችሁ እያየ በምመልስላችሁ ጊዜ በምድር ሕዝቦች ሁሉ ፊት ዝነኞችና የተመሰገናችሁ ትሆናላችሁ።”