ደስታዬ በእርሱ ስለ ሆነ እርሱም በማቀርብለት የተመስጦ ጸሎት ደስ ይበለው።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለኝ፣ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሠኘው።
ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በጌታ ደስ ይለኛል።
ተናገረ፥ አንበጣም፥ ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ መጣ፥
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ።
እንዲህ ያለው ሰው፥ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፤ ቀንና ሌሊትም ያሰላስለዋል።
በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ!
ሕግህ ዘለዓለማዊ ሀብቴ ነው፤ የልቤም ደስታ እርሱ ነው።
ትእዛዞችህን እጠብቃለሁ፤ በሙሉ ልቤም እወዳቸዋለሁ።
ጻድቃን ሆይ! በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ፤ ልበ ቅኖች ሆይ! እልል በሉ!
ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤ ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ።
በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ለስምህ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
ጥበብም ለነፍስህ መልካም መሆኑን ዕወቅ፤ ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ኑሮህ የተቃና ይሆናል፤ ተስፋህም አያቋርጥም።
መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ትደሰታለች፤
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም “ደስ ይበላችሁ!” እላለሁ።
እኔም ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር. ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ።