መዝሙር 101:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድሪቱ የሚገኙትን ክፉዎች ሰዎች በየዕለቱ ጸጥ አሰኛለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ከተማ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ አጠፋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣ በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመፃ የሚያደርጉትን ሁሉ ከጌታ ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥ የምድርን ክፉዎች ሁሉ በማለዳ አጠፋቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ። |
በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥ የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤ እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች።
እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤ አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን በዐይናችን አየን፤ እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል።
የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር አይኖሩም፤ ነገር ግን ተገደው ወደ ግብጽ ይመለሳሉ፤ ወደ አሦርም ሄደው በሥርዓት ንጹሕ ያልሆነ ምግብ ይበላሉ።
ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።