ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያኽል ብዙ ሠራዊትና እንዲሁም በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን።” ንጉሥ ቤንሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ፤
መዝሙር 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛ በክፉ ምኞቱ ይመካል፤ ጌታ ሆይ! እነዚህ ስግብግብ ሰዎች ይጠሉሃል፤ ይሰድቡህማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ በነፍሱ ፈቃድ ይኮራልና፥ ስግብግብም ይረግማል፥ ጌታንም ይንቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ የሠራኸውን እነሆ፥ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ? |
ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያኽል ብዙ ሠራዊትና እንዲሁም በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን።” ንጉሥ ቤንሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ፤
አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ?
ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
ክፉ በሆነው ስግብግብነታቸው ምክንያት በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ እንዲሁም እነርሱን ቀጥቼ ተለይቼአቸው ነበር፤ እነርሱም ወደ ራሳቸው መንገድ ተመለሱ።
በየኰረብታው ላይ ያሉአችሁን መስገጃዎች እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ሬሳዎቻችሁንም በወደቁት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ፈጽሞ እጸየፋችኋለሁ፤
ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።
ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ ይህን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ማድረግ ብቻም ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ሰዎች ያበረታታሉ።
አመንዝራም ቢሆን፥ ማናቸውንም የርኲሰት ሥራ የሚያደርግ ቢሆን፥ ወይም ጣዖት እንደ ማምለክ የሆነ ስግብግብነት ቢሆን፥ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማያገኝ ዕወቁ።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።
እርሱም አንድ ቀን እናቱን እንዲህ አላት፤ “አንድ ሰው አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር በሰረቀሽ ጊዜ ያን የሰረቀሽን ሰው ስትረግሚው ሰምቼሽ ነበር፤ እነሆ ያ ብር በእኔ እጅ ነው፤ እርሱንም የወሰድኩ እኔ ነበርኩ።” እናቱም “ልጄ! እግዚአብሔር ይባርክህ!” አለችው።