ምሳሌ 31:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትሠራው ሁሉ ዋጋ እንዳለው ታውቃለች፤ ማታም ስትሠራ ስለምታመሽ መብራትዋ አይጠፋም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤ በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማትረፍዋን ታስተውላለች፥ መብራትዋ በሌሊት አይጠፋም። |
በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።