Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ብዙ ጊዜ በቀን ሐሩርና በሌሊት ቅዝቃዜ እሠቃይ ነበር፤ በቂ እንቅልፍ ያገኘሁበት ጊዜ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ቀን በሐሩር ሌሊት በቍር ተቃጠልሁ፤ እንቅልፍም በዐይኔ አልዞር አለ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 እንዲህ ስሆን፥ የቀን ሐሩር የሌሊት ቁር ይበላኝ ነበር፥ እንቅልፍም ከዓይኔ ጠፋ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 የቀን ሐሩር፥ የሌ​ሊት ቍር ይበ​ላኝ ነበር፤ ዕን​ቅ​ል​ፍም ከዐ​ይኔ ጠፋ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የቀን ሐሩር የሌሊት ቍር ይበላኝ ነብር እንቅልፍም ከዓይኔ ጠፋ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:40
13 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔርን ቃል በመጀመሪያ የነገሩአችሁን መሪዎቻችሁን አትርሱ፤ የአኗኗራቸውንና የሥራቸውን ውጤት በማስታወስ እምነታቸውን ተከተሉ።


በዚያም አካባቢ፥ በሜዳ ላይ ሌሊት መንጋቸውን እየጠበቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ።


የቀድሞ አባታችን ያዕቆብ ወደ መስጴጦምያ ሸሽቶ ሄደ፤ እዚያም ሚስት ለማግኘት ሲል የበጎች እረኛ ሆኖ አገለገለ።


እነሆ፥ ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የዐማቹን የየትሮንን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ መንጋውንም እየነዳ ከበረሓው ማዶ ወዳለው የእግዚአብሔር ተራራ እየተባለ ወደሚጠራው ወደ ሲና መጣ።


ከበጎችህ አንዱን አውሬ ሲበላው ወዲያው እከፍልህ ነበር እንጂ የእኔ ስሕተት ያለመሆኑን ለማስረዳት ወደ አንተ አምጥቼው አላውቅም፤ በቀንም ቢሆን በሌሊት የተሰረቀ እንስሳ ቢኖር ታስከፍለኝ ነበር።


ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።


መርዘኛ እባብና ጊንጥ በሞላበት፥ አስፈሪ በሆነው በዚያ ሰፊ በረሓ መርቶሃል፤ ምንም ውሃ በማይገኝበት ደረቅ በረሓ ከጽኑ አለት ውሃን አፈለቀልህ፤


እነሆ በዚህ ምክንያት በተራሮች ላይ በእህል፥ በወይን፥ በዘይት፥ ምድር በምታበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶች፥ በሥራቸውም ውጤት ሁሉ ላይ ድርቅን አመጣለሁ።”


የምትሠራው ሁሉ ዋጋ እንዳለው ታውቃለች፤ ማታም ስትሠራ ስለምታመሽ መብራትዋ አይጠፋም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios