የሳዶቅ ዘር የሆነው ሊቀ ካህናት ዐዛርያስም ንጉሡን፥ “ሕዝቡ ዐሥራቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመረ ወዲህ፥ እነሆ፥ በቂ ምግብ አለን፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ ባረከ እነሆ፥ ይህን ሁሉ በብዛት አግኝተናል” አለው።
ምሳሌ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ብታደርግ ጐተራዎችህ በእህል የተሞሉ ይሆናሉ፤ የወይን መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይትረፈረፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ብታደርግ፣ ጐተራህ ሞልቶ ይትረፈረፋል፤ መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐተራህም እህልን ይሞላል፥ መጥመቂያህም በወይን ጠጅ ሞልታ ትትረፈረፋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጐተራህም እህልን ይሞላል። የወይን መጥመቂያህም ወይን ይሞላል። |
የሳዶቅ ዘር የሆነው ሊቀ ካህናት ዐዛርያስም ንጉሡን፥ “ሕዝቡ ዐሥራቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመረ ወዲህ፥ እነሆ፥ በቂ ምግብ አለን፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ ባረከ እነሆ፥ ይህን ሁሉ በብዛት አግኝተናል” አለው።
ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ወይም ሕጉንና ትእዛዞቹን ለመጠበቅ ያከናወነው ሥራ ሁሉ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር በፍጹም ታማኝነትና በመንፈሳዊ ቅናት ስለ ነበር ሁሉም ነገር ተሳካለት።
አሁን ለዘር የሚሆን እህል በጐተራ ባይኖር የወይንና የበለስ፥ የሮማንና የወይራም ተክል ሁሉ ገና ፍሬ ባይሰጥም ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔ በረከትን እሰጣችኋለሁ።”
በእውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ፥ ከነዚህ ታናናሾች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም።”
በከተሞቻችሁ የሚኖሩ ከእናንተ ጋር የተካፈሉት ርስት የሌላቸው ሌዋውያን፥ የውጪ አገር ስደተኞች፥ እናትና አባት የሌላቸው የሙት ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መጥተው ይብሉ፤ ይህን ሁሉ ብታደርጉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምትሠሩት ነገር ሁሉ ይባርካችኋል።