Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 28:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “እግዚአብሔር አምላክህ ጐተራህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ይባርክልሃል፤ እንዲሁም በሚሰጥህ ምድር ይባርክሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ጌታ በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ ላይ በረከቱን ይልካል። ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጎተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:8
22 Referencias Cruzadas  

ይልቅስ ያለ ቅርታ በለጋሥነት ስጥ፤ ይህን ብታደርግ አምላክህ እግዚአብሔር በምትሠራው ሥራና በምታደርገው ድርጊት ሁሉ ይባርክሃል።


ገና ያለፈውን ሰብል በመብላት ላይ እያላችሁ፥ ለአዲሱ ሰብል ቦታ ማስለቀቅ ይኖርባችኋል።


ከሔርሞን ተራራ ወደ ጽዮን ኰረብቶች እንደሚንጠባጠብ ጤዛ ነው፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ የሆነውን ሕይወትና በረከት የሚሰጠው በዚያ ነው።


እንዲህም አለ፦ ‘የማደርገው ይህ ነው፤ ጐተራዎቼን ሁሉ አፈርስና ሌሎች ትልልቅ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያ እህሌንና ንብረቴን ሁሉ ሰብስቤ አከማቻለሁ።


እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?


እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩን በቀን ይሰጣል፤ በሌሊትም የምስጋና መዝሙር አቀርብለታለሁ፤ ወደ ሕይወቴ አምላክ እጸልያለሁ።


በስድስተኛው ዓመት እኔ ምድሪቱን እባርካታለሁ፤ ስለዚህም ለሦስት ዓመት የሚበቃ ሰብል ታስገኛለች፤


አሁን ለዘር የሚሆን እህል በጐተራ ባይኖር የወይንና የበለስ፥ የሮማንና የወይራም ተክል ሁሉ ገና ፍሬ ባይሰጥም ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔ በረከትን እሰጣችኋለሁ።”


ጐተራዎቻችን በልዩ ልዩ ዐይነት እህል የተሞሉ ይሁኑ፤ በመስኮቻችን ላይ የተሰማሩት በጎች በሺህ የሚቈጠሩ ግልገሎችን እየወለዱ ይብዙ።


ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዐይነት ርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?


ስለዚህ ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጐተራዬ ክተቱ’ እላቸዋለሁ።”


አንተ ንጉሤና አምላኬ ነህ፤ የያዕቆብ ዘር ለሆነው ሕዝብህ፥ ድልን የምታጐናጽፍ አንተ ነህ።


“እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዞች ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ታዛዥ ሆነህ ብትገኝ፥ እግዚአብሔር አብዝቶ ስለሚባርክህ እርሱ በርስትነት በሚሰጥህ ምድር በመካከልህ ድኻ አይኖርም፤


“ጠላቶችህ በአንተ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ድል ያደርግልሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ።


“ክፉ ነገር በማድረግ እግዚአብሔርን ስለ ተውክ በምታደርገው ነገር ሁሉ ፈጽመህ እስክትጠፋ ድረስ እርግማንን፥ ሁከትንና ውርደትን ያመጣብሃል።


በከተሞቻችሁ የሚኖሩ ከእናንተ ጋር የተካፈሉት ርስት የሌላቸው ሌዋውያን፥ የውጪ አገር ስደተኞች፥ እናትና አባት የሌላቸው የሙት ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መጥተው ይብሉ፤ ይህን ሁሉ ብታደርጉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምትሠሩት ነገር ሁሉ ይባርካችኋል።


እርሱም፦ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥ በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል።


ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios