ምሳሌ 26:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረዶ በበጋ ወራት፥ ዝናብም በመከር ወራት እንደማያስፈልግ ሁሉ ለሞኝ ክብር አይገባውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣ ክብርም ለሞኝ አይገባውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረዶ በበጋ ዝናብም በመከር እንደማይፈልግ ሁሉ፥ እንዲሁም ለሞኝ ክብር አይገባውም። |
አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ?
ይህ ካልሆነ ግን ከአቤሜሌክ እሳት ወጥቶ የሴኬምንና የቤትሚሎንን ሰዎች ይብላ፤ እንዲሁም ከሴኬምና ከቤትሚሎ እሳት ወጥቶ አቤሜሌክን ይብላ።”
ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።