ምሳሌ 24:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ ሁልጊዜ የሚያስበው ኃጢአትን ስለ ማድረግ ነው፤ ፌዘኛን ሰዎች ሁሉ ይጠሉታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተላላ ዕቅድ ኀጢአት ነው፤ ሰዎችም ቂልነትን ይጸየፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞኝ እቅድ ኃጢአት መሥራት ነው። ሰዎች ፌዘኛውን ይጸየፉታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ በኀጢአት ይሞታል፤ ነፍሰ ገዳይ ሰውን ርኵሰቱ፥ |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።
እግዚአብሔርን በማወቅ ላይ እንቅፋት ሆነው የሚነሡትን ክርክርና ትዕቢት እናፈርሳለን፤ የሰውን ሐሳብ ሁሉ እየማረክንም ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።