ምሳሌ 24:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! መልካም ስለ ሆነ ማር. ብላ፤ የማር ወለላ ለምላስህ ጣፋጭ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ መልካም ነውና ማር ብላ፤ የማር ወለላም ጣዕም ይጣፍጥሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፥ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ማር ብላ፥ ወለላ ጕሮሮህን ያጣፍጥልህ ዘንድ መልካም ነውና። |
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ! እነሆ ወደ አትክልት ቦታዬ ገባሁ፤ ከርቤዬንና የሽቶ አበባዎቼን ለቀምኩ፤ የማር ሰፈፌን ከወለላው ጋር ተመገብኩ፤ የወይን ጠጄንና ወተቴንም ጠጣሁ። ወዳጆቼ ሆይ! በፍቅር እስክትረኩ ድረስ ብሉ፥ ጠጡ።
ከማሩም ጥቂት በእጁ ቈርጦ እየበላ መንገዱን ቀጠለ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱ ቀርቦ ከያዘው ማር. ሰጥቶአቸው በሉ፤ ነገር ግን ሶምሶን ያንን ማር. ያገኘው ከሞተው አንበሳ በድን ውስጥ መሆኑን አልነገራቸውም።
ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ማስማሉን ስላልሰማ፥ የያዘውን በትር በመዘርጋት ወለላውን እየሳበ ጥቂት ማር. በላ፤ ወዲያውኑ ብርታት አግኝቶ ዐይኑ በራ፤