Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 16:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 መልካም ንግግር እንደ ማር. ወለላ ይጣፍጣል፤ ለሰውነትም ፈውስ የሚሰጥ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ደስ የሚያሰኝ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለዐጥንትም ፈውስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፥ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ጣፋጭነቱም የነፍስ መድኀኒት ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 16:24
18 Referencias Cruzadas  

ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደ ሰይፍ ያቈስላል፤ በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል።


እነርሱም ለሚያስተውሉአቸው ሕይወትን፥ ለመላ ሰውነትም ጤንነትን ይሰጣሉ።


ይህን ብታደርግ ለሰውነትህ ጤንነትን፥ ለአጥንቶችህም ጥንካሬን ታገኛለህ።


ትክክለኛ ቃል በምትናገርበት ጊዜ ኲራት ይሰማኛል።


ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል።


ቃልህ እንዴት ጣፋጭ ነው! ከማር ወለላ ይልቅ ይጣፍጣል።


እነርሱ ከንጹሕ ወርቅ የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው፤ ከማር ወለላ ይበልጥ ጣፋጮች ናቸው።


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እኔ በስምህ ተጠርቼአለሁ፤ ቃልህ ወደ እኔ በመጣ ጊዜ በሙሉ ተቀብዬዋለሁ፤ ልቤንም በደስታና በሐሴት ሞላው።


እግዚአብሔር ክፉ ሐሳብን ይጠላል፤ ንጹሕ በሆነ ቃል ግን ደስ ይለዋል።


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥


ተገቢውን ቃል በተገቢው ቦታ መናገር እጅግ ያስደስታል።


ሙሽራዬ ሆይ! ከከንፈሮችሽ የማር ወለላ ይፈስሳል፤ ከአንደበትሽም ማርና ወተት ይፈልቃል፤ የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ ሽቱ ነው።


ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።


ጥበበኛው ተስማሚ የሆኑ ቃላትንም መረመረ፤ ስለዚህ እርሱ የጻፈው ሁሉ እውነትና ትክክል ነው።


እኔም ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር. ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios