ዐመፀኞች መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ስለማይወዱ በግፍ ሥራቸው ይጠፋሉ።
ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤ ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና።
ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኀጥኣን ንጥቂያ ራሳቸውን ያጠፋቸዋል።
ጽድቅን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኃጥኣን ጥፋት ከሩቅ ይመጣል።
የሚያመጡት ችግር በራሳቸው ላይ ይደርሳል፤ በክፉ ድርጊታቸውም ዐናታቸው ይፈጠፈጣል።
እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።
ደግ ሰው በረከትን ያገኛል፤ ክፉ ሰው ግን ዐመፀኛነቱን በመልካም አነጋገር ይሸፍናል።
ጽድቅንና ቸርነትን የሚከተል ሰው ሕይወትን፥ ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።
ወንድሞቻችሁ የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ እንዳሳደድኩ፥ እናንተንም ከፊቴ አሳድዳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
አባቱ ግን ብዝበዛን ስለ ፈጸመ፥ ወንድሙን ስለ ቀማና በሕዝቡ ዘንድ መልካም ያልሆነውን ነገር ስላደረገ በበደሉ ይሞታል።
እናንተ ፍርድን የምታጣምሙና እውነትን ወደ ሐሰት የምትለውጡ ወዮላችሁ!
በእነዚህ ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ሰዎች ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ስለሚመጣ ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።