በጥንቃቄ በወጣ ዕቅድ የሚሠራ ሥራ ትርፍ ያስገኛል፤ ያለ ዕቅድ በችኰላ የሚሠራ ሥራ ግን ያደኸያል።
የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።
የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል።
የትጉህ ዐሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።
ስንፍና ያደኸያል፤ ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤
ሰነፍ አንድ ነገር ለማግኘት አጥብቆ ይመኛል፤ ይሁን እንጂ አያገኝም፤ ትጉህ ሠራተኛ ግን የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል።
ትዕግሥተኛ ብትሆን አስተዋይ መሆንህን ትገልጣለህ፤ ቊጡ ብትሆን ግን ስንፍናህን ታሳያለህ።
ዕውቀት ያልተጨመረበት ትጋት ጠቃሚ አይደለም፤ በችኰላ የሚሮጥ ሰው መንገዱን ይስታል።
በመጀመሪያ ያለ ድካም በቀላሉ የሚገኝ ሀብት በመጨረሻ አይባረክም።
ስስታም ሀብታም ለመሆን ሲጣደፍ ድኽነት በቶሎ የሚመጣበት መሆኑን አይገነዘብም።
ሳያስብ በችኰላ ከሚናገር ሰው ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።
ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ ወዲያ አይስረቅ፤ ይልቅስ ለችግረኞች ይሰጥ ዘንድ ገንዘብ እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካም ነገርን ይሥራ።