ምሳሌ 21:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ደጋግ ሰዎች ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎችን ግን ያስደነግጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርድን ማድረግ ለጻድቅ ደስታ ነው፥ ኃጢአትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን ማድረግ ለጻድቃን ደስታ ነው፤ ጻድቅ ሰው ግን ክፉ በሚሠሩ ዘንድ የረከሰ ነው። |
የአንተን መንገድ አስታውሰው ፈቃድህን በደስታ የሚፈጽሙትን ትረዳቸዋለህ፤ ፈቃድህን መተላለፍን በቀጠልን ጊዜ ግን አንተ ተቈጣኸን፤ ታዲያ እንዴት ልንድን እንችላለን?