ምሳሌ 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ ሰው ቁም ነገር አይናገርም፤ ከጨዋ ሰው ግን የውሸት ንግግር አይጠበቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም አነጋገር ለሞኝ አይሰምርለትም፤ ለገዥ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰነፍ የኩራት አነጋገር አይገባውም፥ ይልቁንም ሐሰተኛ ከንፈር ለመኰንን አይገባውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ የሐሰት ከንፈርም ለጻድቅ አትስማማውም። |
አንተ ግብዝ! አስቀድመህ በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በኋላ፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጒድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።