Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 17:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 መልካም አነጋገር ለሞኝ አይሰምርለትም፤ ለገዥ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆን!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለሰነፍ የኩራት አነጋገር አይገባውም፥ ይልቁንም ሐሰተኛ ከንፈር ለመኰንን አይገባውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሞኝ ሰው ቁም ነገር አይናገርም፤ ከጨዋ ሰው ግን የውሸት ንግግር አይጠበቅም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ የሐሰት ከንፈርም ለጻድቅ አትስማማውም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 17:7
15 Referencias Cruzadas  

ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።


አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።


በሞኝ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ የሰለለ የሽባ ሰው እግር ነው።


እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።


በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።


የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ ‘ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣


በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ፣ ትዕቢትንና ንቀትን የተሞሉ፣ ዋሾ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።


ትዕቢተኛ ዐይን፣ ሐሰተኛ ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆች፣


እግዚአብሔር ሐሰተኛ ከንፈርን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ደስ ይለዋል።


ሞኝ ተንደላቅቆ መኖር አይገባውም፤ ባሪያ የመሳፍንት ገዥ ከሆነማ የቱን ያህል ይከፋ!


ጥበብ ለቂል በጣም ሩቅ ናት፤ በከተማዪቱ በር ሸንጎ ላይም መናገር አይችልም።


በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣ ክብርም ለሞኝ አይገባውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios