ምሳሌ 17:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ ኀዘንተኛ ሰው ግን አጥንቱን ያደርቃል። |
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ሐዘን ወደ መዳን የሚመራ በንስሓ የሚገኘውን ለውጥ ስለሚያስገኝ ጸጸትን አያስከትልም፤ ዓለማዊ ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።