ማስተዋል የጐደለው ሰው ለሌላ ሰው ዋስ ይሆናል፤ ራሱንም ተያዥ አድርጎ ይሰጣል።
ልበ ቢስ ሰው ሰው ቃል በመግባት እጅ ይመታል፤ ለወዳጁም ዋስ ይሆናል።
አእምሮ የጐደለው ሰው አጋና ይመታል፥ በባልንጀራውም ፊት ይዋሳል።
አላዋቂ ሰው አጋና ይመታል፥ ለባልንጀራውም ዋስ እንደሚሆን በራሱ ደስ ይለዋል።
የማታውቀውን ሰው ዕዳ ለመክፈል ዋስ ብትሆን፥ በችግር ላይ ትወድቃለህ፤ ዋስ መሆን ቢቀርብህ ግን የተሻለ ነው።
ማንም ሰው ለእንግዳ ሰው ከተዋሰ፥ ልብሱን ውሰድ፤ ለማይታወቀው ሰው መያዣ እንዲሆን አንተ ዘንድ አስቀምጠው።
ለሀብታሞች ስጦታ የሚሰጥ፥ ወይም ሀብት ለማግኘት ብሎ ድኾችን የሚጨቊን ሰው ይደኸያል።