Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 22:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ለሀብታሞች ስጦታ የሚሰጥ፥ ወይም ሀብት ለማግኘት ብሎ ድኾችን የሚጨቊን ሰው ይደኸያል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለራሱ ጥቅም ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለሀብታም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ድሃን የሚቀማ ገንዘቡን ብዙ ያደርግለታል፥ በችግሩ ጊዜም ለባለጠጋ ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 22:16
14 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


ድኾችን የሚጨቊን መሪ ሰብልን እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው።


ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።


ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ ‘አባት አብርሃም ሆይ! እባክህ ራራልኝ! በዚህ በእሳት ነበልባል ውስጥ በብርቱ እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ አልዓዛርን ላክልኝ!’


ስስታም ሀብታም ለመሆን ሲጣደፍ ድኽነት በቶሎ የሚመጣበት መሆኑን አይገነዘብም።


በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios