ምሳሌ 15:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለስላሳ አነጋገር ሕይወትን ይሰጣል። ተንኰል የተሞላበት አነጋገር ግን መንፈስን ይሰብራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፥ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የሚጠብቀው ግን የዕውቀት መንፈስን ይሞላል። |
ከእውነተኛ እግዚአብሔርን የማምለክ ትምህርት ጋር ተስማሚ የሆነውን፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ንጹሕ ቃል ትቶ የተለየ ትምህርት የሚያስተምር ማንም ሰው ቢኖር፤
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’