ይህ ሁሉ የደረሰባቸው እነርሱ ልጆች የሌላቸው መኻኖች ሴቶችን በመበዝበዛቸውና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ምንም ርኅራኄ ባለማሳየታቸው ነው።
ምሳሌ 15:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ይደመስሳል፤ ባልዋ የሞተባትን ሴት ድንበር እንዳይገፋ ይጠብቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤ የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የትዕቢተኞችን ቤት ይነቅላል፥ የባልቴትን ዳርቻ ግን ያጸናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ የመበለቷን ወሰን ግን ያጸናል። |
ይህ ሁሉ የደረሰባቸው እነርሱ ልጆች የሌላቸው መኻኖች ሴቶችን በመበዝበዛቸውና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ምንም ርኅራኄ ባለማሳየታቸው ነው።
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ?
መልካም ማድረግንም ተማሩ፤ ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ የተጨቈኑትን ታደጉ፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት ጠብቁ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ ስሙ።”
እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።
“እግዚአብሔር አምላክህ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ለአንተ በተሰጠው ድርሻና በጐረቤትህ መካከል በቀድሞ ትውልድ የተተከለውን የድንበር ምልክት አታፍርስ።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ ሃይማኖት “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።