ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
ምሳሌ 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታም በገንዘብ ሕይወቱን ለማዳን ይጣጣራል፤ ድኻ ግን የሚወሰድበት ሀብት ስለሌለው አይጨነቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፥ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም። |
ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
አንዳንድ ሰዎች ምንም ሳይኖራቸው ሀብታም መስለው ለመታየት ይጥራሉ፤ ሌሎች ደግሞ ብዙ ሀብት እያላቸው፥ ምንም ሀብት እንደሌላቸው መስለው ይኖራሉ።
ከእነዚያ ሰማኒያ ሰዎች መካከል በተለይ ዐሥሩ ሰዎች “እባክህ አትግደለን! እኛ በእርሻ ውስጥ የደበቅነው ብዙ ስንዴ፥ ገብስ፥ የወይራ ዘይትና ማር. አለን” ብለው እስማኤልን ለመኑት። እርሱም ምሕረት አደረገላቸው።