ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።
ዘኍል 7:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያው ቀን ስጦታውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበ ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበ ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ። |
ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በዐሥራ ሁለት ተከታታይ ቀኖች ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አለቆች አንዱ መሠዊያው ለሚቀደስበት ክብረ በዓል የሚሆን መባ ያቀርቡ ዘንድ ንገራቸው።”
ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥