ዘኍል 5:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ የዱቄቱን መባ ከሴትዮዋ እጅ ወስዶ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ የተለየ መሥዋዕት ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቅርበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቍርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቁርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም የቅንዐቱን መሥዋዕት ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፤ ያንም መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቍርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤ |
ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ ስለ እርስዋ የሚፈልገውንም አንድ ኪሎ የገብስ ዱቄት ቊርባን ያምጣ፤ የቅናት ቊርባን ማለት በደልን የሚገልጥ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት።
ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ።
ከዚህም በኋላ ከእህሉ ቊርባን አንድ እፍኝ ወስዶ የመታሰቢያ ቊርባን ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በመጨረሻም ሴትዮዋ ውሃውን እንድትጠጣው ያድርግ።