Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 5:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቍርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቍርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቁርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ካህኑ የዱቄቱን መባ ከሴትዮዋ እጅ ወስዶ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ የተለየ መሥዋዕት ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቅርበው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ካህ​ኑም የቅ​ን​ዐ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ከሴ​ቲቱ እጅ ይወ​ስ​ዳል፤ ያንም መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ያመ​ጣ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 5:25
6 Referencias Cruzadas  

ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታኖረዋለህ፤ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ።


ሁሉንም በአሮንና በልጆቹ እጆች ላይ አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ወዘወዛቸው።


የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዓት ቍርባን ነውና፥ ኃጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት።


ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፥ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ ለቅንዓት ቍርባን፥ ያኖራል፤ በካህኑም እጅ እርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል።


እርግማን የሚያመጣውንም መራራ ውኃ ለሴቲቱ ያጠጣታል፤ የእርግማኑም ውኃ በገባባት ጊዜ መራራ ይሆናል።


ካህኑም ከእህሉ ቍርባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፥ ከዚያም በኋላ ለሴቲቱ ውኃውን ያጠጣታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos