ዘኍል 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ባለው ዕጣን፥ ዘወትር በሚቀርበው በእህሉ ቊርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ኀላፊነት ይኖረዋል፤ እንዲሁም የመገናኛው ድንኳን በሙሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሁሉ ይጠብቃል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ባለው ዕጣን፣ ዘወትር በሚቀርበው በእህል ቍርባንና በቅብዐ ዘይቱ ላይ ኀላፊነት ይኖረዋል፤ እንደዚሁም ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ መቅደሱንና ዕቃዎቹን ጭምር ይጠብቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት በጣፋጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቍርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድንኳኑን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይጠብቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት በጣፋጩም ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቍርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይጠብቃል። |
የቅባቱ ዘይትና ለተቀደሰው ስፍራ የሚሆነው መዓዛው ጣፋጭ የሆነ ዕጣን፤ ልክ እኔ አንተን ባዘዝኩት ዐይነት እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ።”
“በድንኳኑ ውስጥ ያለው መብራት ዘወትር ሲበራ እንዲኖር ለማድረግ ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት ያመጡልህ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ።
“ካህኑ በሚሾምበት ቀን መጠኑ በየዕለቱ ከሚቀርበው የእህል መባ ጋር እኩል የሆነ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ፤ እርሱም ከፊሉ ጠዋት፥ ከፊሉ ደግሞ ማታ መሥዋዕት ሆኖ ይቅረብ፤
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን የክርስቶስ አገልጋዮች እንደ ሆንን የእግዚአብሔርንም ምሥጢር የመግለጥ ኀላፊነት የተሰጠን ባለ ዐደራዎች እንደ ሆንን አድርጎ ሊቈጥረን ይገባል።
ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።
በዐደራ የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ መንጋውን የምትጠብቁትም በግድ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገው ዐይነት፥ በፈቃደኛነት ይሁን፤ ለገንዘብ በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ይሁን።