ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የንጉሡንና የባለሥልጣኖቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ ልብ አነሣሣ።
ዘኍል 36:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም የሰለጰዓድ ሴት ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። |
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የንጉሡንና የባለሥልጣኖቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ ልብ አነሣሣ።
ሙሴም ይህን ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ ያን ሰው ከሰፈር አወጡና በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
እነርሱም ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው “እንደ ወንዶች ዘመዶቻችን የርስት ድርሻ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ሙሴን አዞታል” አሉአቸው። ስለዚህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለእነርሱ ከወንዶች ዘመዶቻቸው ጋር የርስት ድርሻ ተሰጣቸው፤