ዘኍል 34:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ ምልክት ይደርሳል፤ የድንበሩም መጨረሻ ጸዳድ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሖር ተራራ እስከ ሌቦ ሐማት እንደዚሁ አድርጉ፤ ከዚያም ወሰኑ እስከ ጽዳድ ይሄድና መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ የወሰን ምልክት ታደርጋላችሁ የድንበራችሁም መጨረሻ በጽዳድ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተራራው እስከ ተራራው ድረስ ይሆንላችኋል፤ እስከ ኤማትም ይደርሳል፤ የዳርቻውም መውጫ በሰረደክ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ ምልክት ታመለክታላችሁ የዳርቻውም መውጫ በጽዳድ ይሆናል፤ |
በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር፤
ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።
ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ከቂርያትይዓሪም ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደቡብ በኩል እስከ ግብጽ ግዛት ድንበር፥ በሰሜን እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ በመላው እስራኤል የሚገኘውን ሕዝብ በአንድነት ሰበሰበ።
ነገር ግን የባቢሎን ሠራዊት ከኋላቸው ተከትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ደረሱበትና ሴዴቅያስን ማረኩት፤ ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሥ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያን ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር በሐማት ግዛት ሪብላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ውስጥ ነበር፤ ንጉሥ ናቡከደነፆርም እዚያው በሴዴቅያስ ላይ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈበት።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእናንተ ላይ የሌላ ሕዝብ ኀይል አስነሣባችኋለሁ፤ እርሱም በሰሜን ከሐማት መግቢያ በር ጀምሮ በደቡብ እስከ አረባ ሸለቆ ድረስ ዘልቆ ያስጨንቃችኋል።”